Telegram Group & Telegram Channel
ጾመ ሐዋርያት

በወርኃ ሰኔ የሚጾም በመሆኑ ይህ ጾም በተለምዶ የሰኔ ጾም በመባል ይታወቃል፡፡ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ ጾመ ሐዋርያትን ለመጀመሪያ ጊዜ የጾሙት ቅዱሳን ሐዋርያት ሲሆኑ የጾሙበትም ዋና ምክንያት በሃምሳኛው ቀን ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ስለተቀበሉና እግዚአብሔር ስላደረገላቸው መልካም ነገር ለማዘከር ነው፡፡

ጾመ ሐዋርያት በዓለ ጰራቅሊጦስ በመጀመሪያው ሰኞ ይውላል፡፡ ጌታችን አምላካችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ሥጋዌው ደቀ መዛሙርቱን ይህን ጾም እንደሚጾሙት እንዲህ ተናግሮ ነበር፡፡ ‹‹በዚያን ጊዜ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ቀርበው። ‹‹እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ እንጾማለን፥ ደቀ መዛሙርትህስ ለምን አይጾሙም? አሉት፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፬)  ደቀ መዛሙርቱ ይህንን በጠየቁት ጊዜ ጌታችን እንዲህ ብሎ መልሶላቸው ነበር፡፡ ‹‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ የሙሽራው ሚዜዎች ሙሽራው  ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ አይችሉም፤ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወራት ይመጣል፤ ያንጊዜም ይጾማሉ፡፡›› (ማቴ.፱፥፲፭)
 
በቅዱሳን ሐዋርያት ላይ ያደረው ጸጋ መንፈስ ቅዱስና ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በእኛም ላይ እንዲያድር፣ ከቅዱሳን ሐዋርያቱ በረከት እንድንሳተፍ፣ አገልግሎታችን በስኬት እንዲቃና እና ወርኃ ክረምቱ በሰላም ያልፍልን ዘንድ ጾመ ሐዋርያትን መጾም አስፈላጊ ነው፡፡ ከጸሎትና ምጽዋትን መንፈሳዊ እድገትን በጾም አስምረን ከራሳችንን እና ከእግዚአብሔር አምላካችን ጋር የምንታረቅበት እንዲሆንልን የቅዱሳን አባቶቻችን ሐዋርያት በረከትና ጸሎትም አይለየን፡፡
 
የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም እና የቅዱሳን ሐዋርያት  አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!
 
tg-me.com/finote_kidusan/348
Create:
Last Update:

BY ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/finote_kidusan/348

View MORE
Open in Telegram

ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Mr. Durov launched Telegram in late 2013 with his brother, Nikolai, just months before he was pushed out of VK, the Russian social-media platform he founded. Mr. Durov pitched his new app—funded with the proceeds from the VK sale—less as a business than as a way for people to send messages while avoiding government surveillance and censorship.

Traders also expressed uncertainty about the situation with China Evergrande, as the indebted property company has not provided clarification about a key interest payment.In economic news, the Commerce Department reported an unexpected increase in U.S. new home sales in August.Crude oil prices climbed Friday and front-month WTI oil futures contracts saw gains for a fifth straight week amid tighter supplies. West Texas Intermediate Crude oil futures for November rose $0.68 or 0.9 percent at 73.98 a barrel. WTI Crude futures gained 2.8 percent for the week.

ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ from pl

Telegram ፍኖተ ቅዱሳን ꜰɪɴᴏᴛᴇᴋɪᴅᴜsᴀɴ
FROM USA